|
ሰላምታ ለአውሮፓ ህዝብ!
አባቶቻችሁ! . . . በምድርም በሰማይ አቆራርጠው መጥተው፣ በአፍሪካ . . . መጽሀፍ ቅዱስን በገፍ አሰራጭተው ለቀደምቶቻችን፣ እንደዚህ እያሉ፣ ፍቅር ነበር ሰብከው: ጉንጭህን ለሚመታ ደግሞ፣ ሁለተኛውን ስጠው፣ መጎናጸፊያህንም ለሚወስድ፣ እጄ ጠባብህን ደግሞ አትከልክለው . . . አሁንም! . . . የእነሱ ልጅ ልጆች. . . እኛ! የአባቶቻችሁ ልምድ ወራሽ፣ ህመምተኛ! የስየል፣ የእርዛት፣ የግፍ ሰለባዎች፣ ባገር በቀል ጨቋኝ፣ የዕድሜ ልክ ገዢዎች፣ ባህር አቆራረጠን፣ በአረጁ ጀልባዎች ፣ አስፈሪ ማዕበል፣ የተፋን ግልቶች፣ በጨዋማው ንፋስ፣ በድንበር ጠባቂ ወታደሮቻችሁ፣ በጥፊ ተላግተን፣ መለመላችንን ቆመን ከፊታችሁ፣ ከሞት የተረፍን . . .ይዘው እያወጡ ዘይት እንደገቡ ብርቅ ወፎቻችሁ! ይኸው መጨረሻ፣ ማንኳኳት ይዘናል፣ ደርሰን ከበራችሁ፣ የተስፋ ቅራሬ፣ ተስፋ በመሰነቅ፣ እንዳልተረሷችሁ፣ እኒያ! እኒያ! እኒያ! የፍቅር ቃላቱ . . . ለእኛ አባቶች የእናንት ያኔ የሰበኩቱ። |
Greetings to the people of Europe!
Over land and sea, your fathers came to Africa and unpacked bibles by the thousand, filling our ancestors with words of love: if someone slaps your right cheek, let him slap your left cheek too! if someone takes your coat, let him have your trousers too! now we, their children’s children, inheriting the words your fathers left behind, our bodies slapped and stripped by our lifetime presidents, are braving seas and leaky boats, cold waves of fear – let salt winds punch our faces and your coast-guards pluck us from the water like oily birds! but here we are at last to knock at your front door, hoping against hope that you remember all the lovely words your fathers preached to ours. |